የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መከበሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እርስ በርሳቸው እንዲተዋወቁ፣ ባህላዊ እሴቶቻቸውን፣ መልካም ተሞክሮዎቻቸውንና ልምዶቻቸውን እንዲለዋወጡ የሚያግዛቸዉ መሆኑን አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ የልዑካን ቡድን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚከበረዉ 20ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም ሆሳዕና ከተማ ገብቷል፡፡
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አፈጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የክልሉ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባባል አድርገዉላቸዋል፡፡
20ኛዉየኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማእከላዊ ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት» በሚል መሪ ቃል ህዳር 29 ቀን በሃገር አቀፍ ደረጃ በሆሳዕና ከተማ ይከበራል፡፡
በያለዉ ጌታነህ