የትውልድ ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ላይ እየታየ የመጣውን የውጤት ማጣት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለ19 ተከታታይ ክፍሎች የዘለቀ የቀድሞ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና ባለ ድርሻ አካላት የተሳተፋበት የቀጥታ ስርጭት ውይይቶች ማድረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከታታይ እና ሁሉን አሳታፊ የውይይት መድረክም ከፍ በማድረግ “ለአትሌቲክሳችን ትንሳዔ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
በፓናል ውይይቱ ላይም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህንን ጨምሮ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካዮች፤ አሰልጣኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።
በዘላለም አቢይ