ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የብሔሮ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጥያቄ ምላሽ እያገኘ ነው – የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር

You are currently viewing ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የብሔሮ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጥያቄ ምላሽ እያገኘ ነው – የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር

AMN – ሕዳር 28/ 2018 ዓ.ም

20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲምፖዚየም እና የምክክር መድረክ የበዓሉ አስተናጋጅ በሆነው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

የመድረኩ በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር አፈ- ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ፤ ይህ በዓል ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ዜጐችን ለማቀራረብ ትልቅ ድርሻ አለው ነው ያሉት ።

በዓሉ ብሄሮችና ብሄረሰቦች እሴቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትን መድረክ ለማስተናገድ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል ሲሉ ተናግረዋል ።

የበዓሉ የክብር እንግዳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በዓሉ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የብሔሮ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል ።

አንዱ የቤት ልጅ አንዱ የእንጀራ ልጅ የማይሆንባት ዴሞክራሲዊ መግባባትን ባህል ለማድረግ በጋራ እና በእኩልነት በመቆም ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን አቶ አገኘሁ ገልፀው፤ ይህንንም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተዋል ።

የመንግስት ስልጣን የሚያዘው በዲሞክራሲ ምርጫ ብቻ ነው ያሉት አቶ አገኘሁ ዘንድሮ የሚካሄደው ሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ ተአማኒ፣ አሳታፊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ይሰራል ብለዋል ።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ይህንን በዓል ሲያከብሩ በሕገ – መንግስቱ ጥላ ስር የዓመታት ጥያቄዎቻቸውን እየተፈቱ የመጡበት ነው ብለዋል፡፡

የዚህ በዓል አስተናጋጅ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራዎችን ጀምሮ የማጠናቀቅ 24/7 የስራ ባህልን ያረጋገጠበት መሆኑንና አንስተዋል ።

በሲምፓዚየሙ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ የኢፊድሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልል ርእሰ መስተዳድር እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review