በኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ የመልካ ሶር የኢሬቻ በዓል አባገዳዎች: ሃደ ሲንቄዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ ተከብሯል።
የኢሉአባቦር ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ደበላ ለኤኤምኤን ዲጂታል እንደተናገሩት የመልካ ሶር የኢሬቻ በዓል የዞኑ ነዋሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች በተገኙበት ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በድምቀት ተከብሯል።
የዞኑ ህዝብ የክረምት ወራትን መጠናቀቅ ተከትሎ ለረጅም አመታት በመልካ ሶር በመገኘት ለፈጣሪዉ ምስጋና ሲያቀርብ እንደነበረም ገልጸዋል።
ኢሉአባቦር ዞን ካለዉ የአየር ጸባይና ከክረምት ወቅት መራዘም ጋር በተያያዘ በአሉ በየአመቱ በህዳር ወር መጨረሻ ላይ ይከበራል።
የዘንድሮዉ የኢሬቻ በዓል ሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ ሃርሰዲ የኢሬቻ በአልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።
በወንድማገኝ አሰፋ