20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መዲና በሆነችው ሆሳዕና ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የዋዜማ ዝግጅትና ሲምፖዚየም በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በሲምፖዚየሙ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፋት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከተራና ትንንሽ ሀሳቦች ወጥተን የተጀመረውን ኢትዮጵያን ትልቅ የማድረግ ህልም ለማሳካት በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል::
አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ አክለው እንዳሉት የዘንድሮው በዓል ኢትዮጵያ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ባሳካችበትና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ይፋ ባደረገችበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርዋል ብለዋል፡፡
20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ሲሆን “የምክክር ቀን” በሚል በተሰየመው የዋዜማ ሲምፖዚየም ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አመራሮች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች፣ የክልሎች ርዕሰ መስተዳድር፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እና የፌዴራል መንግሥ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል ።
በአንዋር አህመድ