የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የቅኝት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል

You are currently viewing የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የቅኝት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
  • Post category:ጤና

AMN ሕዳር 28/2018

የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የቅኝት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ ገለፁ።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ እንዳሉት፤ ኢንስቲትዩቱ የህብረተሰብ ጤናና አደጋ ቁጥጥር፣ የበሽታዎች ቅኝት፣ ዝግጁነትና ምላሽ የመስጠት ሥራ ያከናውናል።

የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር፣ የላቦራቶሪ አቅም ግንባታና የህብረተሰብ ጤና ምርምር ሥራዎችን እንደሚያከናውን ገልፀዋል።

የማርበርግ ቫይረስ በሽታን የመከላከልና የመቆጣጠር፣ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለይቶ የመከታተል እንዲሁም የቅኝት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በመግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ ለህብረተሰቡ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን የማስገንዘብ እንዲሁም ንክኪን የመቀነስ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ብሔራዊ ግብረ ኃይልና የክስተት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የቤት ለቤትና የማህበረሰብ ቅኝት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የቤት ለቤት ቅኝት መደረጉንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው የላቦራቶሪ የመመርመር አቅምን በማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበር ራሱን ከማርበርግ ቫይረስ መከላከል እንዳለበት ማስገንዘባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ማንኛውም ሰው የበሽታውን ምልክቶች ሲያስተውል በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም ሊሄድ እንደሚገባም እንዲሁ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review