የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፊሶን ሪል እስቴት እየገነባቸው ያሉትን 1ሺህ ቤቶችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የቤት አቅርቦትን ለመጨመር በግሉ ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ዛሬ ፊሶን ሪል እስቴት እየገነባቸው ያሉትን 1,000 ቤቶች ተዘዋውረን ተመልክተናል።
እየተገነቡ ያሉት ቤቶች የከተማችንን ደረጃ ለማሻሻል የምንተገብረውን የግንባታ ስታንዳርድ የሚያሟሉ፣ ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆናቸውን በጉብኝታችን አይተናል። ይህ ደግሞ ለኮፕ 32 ተሳታፊዎች አገልግሎት ለመስጠት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው።
በዘርፉ የተሰማራችሁ የከተማችን አልሚዎች፣ እየገነባችሁ ያላችሁና ለኮፕ 32 እያደረጋችሁ ያለውን አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅት በየክፍለ ከተማችሁ ብታሳውቁ የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት እና ጉባኤዉንም የበለጠ ዉጤታማ ለማድረግ ያግዛል።
ለጉባኤው ወደ አገራችን የሚመጡ እንግዶቻችንን በትብብር ለማስተናገድ እና ለጉባኤዉ ዉጤታማነት በጋራ እንስራ ፣ ከወዲሁ እንዘጋጅ በማለት ለአልሚዎች ጥሪያችንን እናቀርባለን ሲሉ ገልጸዋል።