የአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆን በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

You are currently viewing የአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆን በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

AMN – ሕዳር 29/2018 ዓ.ም.

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆን በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ ውይይት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አምራቾች ጋር እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፥ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፥ የከተማዋ መሠረተ ልማት አቅራቢና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፥ አምራቾችና ተወካዮቻቸው ተሳትፈዋል።

የውይይት መድረኩም የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታማነትን ለማሳደግ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችና በሚደረግላቸው ድጋፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 760 አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙ እና ከእነዚህ ውስጥም 410 ያህሉ ተኪ ምርት የሚያመርቱ ሲሆኑ 43 ደግሞ ወደ ውጪ በመላክ የውጪ ምንዛሬ የሚያስገኙ መሆናቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review