“ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ 2ዐኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አባቶቻችን ደም የወረስነውን ነጻነት በብልጽግና ማጽናት ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንነው ያስገነዘቡት፡፡
ብልጽግናን ማሳካት ፈታኝ ሒደት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወረስነው ነፃነት ብቻ ሳይሆን የተሸከምነውን የትውልድ አደራ ጭምር ማሰብ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ አንዱ ከፍ ሌላው ዝቅ ብሎ ሳይሆን በወንድማማችነትና በመደመር እሳቤ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንድናሻገር መትጋት ይኖርብናልም ብለዋል፡፡
በእጅጉ ልንጠቀምበት የሚገባ በርካታ ሀብቶች ያላት ሀገር በመሆኗ ይህ ትውልድ ችግሯን ብቻ ሳይሆን አቅሟን ፈልፍሎ በማውጣት መቀበል ብቻ ሳይሆን መስጠትም ይገባዋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፡፡
በበረከት ጌታቸው