በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በአንድነት እንዲደምቁና እንዲመክሩ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል

You are currently viewing በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በአንድነት እንዲደምቁና እንዲመክሩ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል

AMN ህዳር 29/2018

የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል መግባባቶችን በማጠናከር የሀገረ መንግስት ግንባታን ለማሳለጥ እንዲሁም ሁላችንም በአንድነት እንድንደምቅና እንድንመክር ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በሆሳዕና ከተማ በአቢዬ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስቴዲዬም በድምቀት በተከበረው በዓል ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የልዩነት መነሻ በሆኑ ታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ዜጎች መክረው ዘክረው የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ለማስቻል የጋራ ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ለማኖር በዓሉ የድርሻውን ማበርከቱን ተናግረዋል።

የሀገረ መንግስት ቅቡልነትን ከፍ ለማድረግ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ሒደት ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በዓሉ መከበሩ የምክክር ሒደቱን ፍሬያማ እንደሚያደርገው ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል ሁሉም ያሏቸውን ልዩ ልዩ ባሕላዊ ትውፊቶች፣ እሴቶቻቸውንና ልምዶቻቸውን የሚለዋወጡበት ዕድል ማመቻቸቱንም ተናግረዋል።

የዘንድሮ የብሔ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል የዘመናት ቁጭት መቋጫ፥ የአዲስ ንጋት ማብሰርያ፥ የማንሰራራት ዘመን ምልክት እና አሻራ የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በተበሰሩበት ዘመን የተከበረ መሆኑ በዓሉን የተለየ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review