ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች

You are currently viewing ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች

AMN ህዳር 29/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቢሮ አባል በመሆን በስምምነት ተመርጣለች።

ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና የተመረጠቸው በጄኔቫ ስዊዘርላንድ በተካሄደው የምክር ቤቱ ድርጅታዊ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቡድንን በመወከል ለአንድ አመት ያህል በዚህ የመሪነት ሚና እንደምታገለግል ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ መመረጧን ተከትሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋብ ክበበው ዳካ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review