ከ17 ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃዎችና 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ ተወገደ

You are currently viewing ከ17 ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃዎችና 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ ተወገደ

AMN ህዳር 29/2018 ዓ.ም

ህገወ-ወጥ ጫት ማስቃሚያ ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ በተደረገው ፍተሻ ከ17 ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃዎችና 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ በመገኘቱ ተሰብስቦ በህግ አግባብ መወገዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ከሐምሌ 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2018 ዓ/ም በምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ በፔንሲዮኖች፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶችና በህገ-ወጥ ጫት ማስቃሚያ ቤቶች ላይ በህግ አግባብ በተደረገ ፍተሻ 17ሺ 95 የሺሻ ዕቃዎች፣ 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ እና 100 ኪሎ ግራም ጫት በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እንዲወገድ ተደርጓል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ እንደተናገሩት የዜጎችን ሠላም የሚያውኩ እና ለወንጀል መስፋፋት መንስኤ የሆኑ አዋኪ ድርጊቶችን አስቀድሞ ለመከላከል መምሪያቸው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆንኑ ገልፀዋል፡፡

አስቀድሞ በተደረጉ ጥናቶች ተገቢውን መረጃና ማስረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ ተግባር በመቀየር የወንጀል መንስኤ በሆኑ ደርጊቶች ላይ ተከታታይነት ያለው እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ አስታውሰው ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪቀረፍ እርምጃችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review