ማንችስተር ዩናይትድ ዎልቭስን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ ዎልቭስን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

AMN ኅዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም

በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጪ ዎልቭስን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 4ለ1 አሸንፏል።

በሞሌንዩ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቡርኖ ፈርናንዴዝ በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን አስመዝግቧል።

ብሪያን ምቡሞ እና ሜሰን ማውንት ሌሎች ግቦችን አስገኝተዋል።

ብሪያን ምቡሞ ለክለቡ ያስቆጠረውን ግብ ብዛት ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።

የወልቭስን ብቸኛ ግብ ቤሌጋርድ ማስቆጠር ችሏል።

ድሉን ተከትሎ ዩናይትድ በ25 ነጥብ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በፕሪምየር ሊግ ከሜዳ ውጪ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ ሲያሸንፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ከ15 ጨዋታ ሁለት ነጥብ ብቻ የያዘው ዎልቭስ የደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛል።

አራት ጨዋታ የመራው አዲሱ አሰልጣኝ ሮብ ኤድዋርድስ ሁሉንም ተሸንፏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review