ከባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing ከባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

‎AMN ኅዳር 30/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አባሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:-

‎1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣

‎2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣

‎3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣

‎4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና

‎5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም ‎የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታውቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review