ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የደኅንነት አገልግሎት የሚውል የሩት ሰርተፊኬት አገልግሎት ተጀመረ

You are currently viewing ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የደኅንነት አገልግሎት የሚውል የሩት ሰርተፊኬት አገልግሎት ተጀመረ

‎AMN ሕዳር 30/2018 ዓ.ም

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ደኅንነት አገልግሎት የሚውል የሩት ሰርተፊኬት አገልግሎት አስጀምሯል፡፡

‎የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓቱ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከጥቃት የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚውሉ ዲጂታል ሰርተፊኬቶችን ለማምረት የሚውል የሩት ሰርተፊኬት መሰጠት መጀመሩን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

‎በመግለጫው ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ኢትዮጵያ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን በማገባደድ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን መጀመሩዋን ገልጸዋል።

‎የሕዝብ አገልግሎቶች፣ የፋይናንስ ተሳትፎ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በታመኑ ዲጂታል ስርዓቶች የሚከናወኑበትን እድል እየፈጠረ ይገኛልም ብለዋል፡፡

‎ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘውም ለፋይዳ መታወቂያ ደህንነት የሚውል የዲጂታል ሰርተፊኬት አገልግሎት መጀመሩ ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እምነት የሚጣልበት እና ሁሉን አቀፍ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለመስጠት ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡

‎የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ በበኩላቸው፣ አገልግሎቱ ክፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግበት እና የደህንነት ማስጠበቂያ ዲጂታል ቁልፎች የሚፈጠሩበት እንዲሁም የሚንቀሳቀሱበት መሆኑን አስረድተዋል።

‎እነዚህ ቁልፎች በዲጂታል መታወቂያው ላይ ያለውን የማንነት መረጃ ለመጠበቅ ጥቅም ላይ የሚውል የመተማመኛ ዲጂታል ፊርማ ለማዘጋጀት ይጠቅማሉ ብለዋል፡፡

‎የማንነት ስርቆትን መከላከል፡ ትክክለኛ ግለሰብን የማስመሰል፣ የማጭበርበር እና የማንነት መረጃን አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል ይረዳል ብለዋል ።

ይህም የሀገራችንን ዲጂታል ምህዳር ተዓማኒነት ለማጠናከር እና የዜጎችን የዕለት ተእለት ሕይወት የሚደግፉ ዲጂታል አገልግሎቶችን አስተማማኝ መሠረት ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን አቶ ዮዳሔ ገልፀዋል፡፡

‎በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review