ዲጂታል ኢኮኖሚን መገንባት ምርጫ ሳይሆን ብልጫ ነው

You are currently viewing ዲጂታል ኢኮኖሚን መገንባት ምርጫ ሳይሆን ብልጫ ነው

AMN ሕዳር 30/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ሁለተኛውን የኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ጉባኤን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ተስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዲጂታል ኢኮኖሚን መገንባት ምርጫ ሳይሆን ብልጫ ነው ብለዋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በውጤታማነት መተግበራችን፣ ለዜጎች ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎቶችን ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር፣ የዕለት ከዕለት የኑሮ እንቅስቃሴን እያቀለለ ይገኛል።

በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክና የዲጂታል ግብይት ሥርዓትን ተመራጭ የክፍያ መንገድ እንዲሆን አስችሏል። ይሄም የሕዝብን ኑሮና የመንግሥትን አገልግሎት ከምርጫም በላይ ብልጫ ያለው እንዲሆን ያስችለዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በተዘረጋው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ውስጥ፣ በየዓመቱ ከ18.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ይሄንን ስኬት በላቀ መልኩ በማስቀጠል ሁሉን አቀፍ ብልፅግናን የማሳካት ግብ የያዘውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት አጽድቀናል ብለዋል፡፡

ስትራቴጂው ዲጂታል መሠረተ ልማትን የማጠናከር፣ ተደራሽነትን ብቻ ሳይሆን አጠቃቀምን ለማስፋት ክሂሎትን የመገንባት እና ችግር ፈቺ ፈጠራን የማበረታታት ዓላማ ያለው በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁሉም ሚናውን ሊወጣ ይገባል።

ከዲጂታል ተደራሽነት ወደ ጋራ ብልፅግና የጀመርነውን ጉዞ ለማሳካት፣ የመደመር መንግሥት በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በእመርታ መርሕ እንደሚተጋ አረጋግጣለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review