የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በእስካሁን ሂደት የተከናወኑ ተግባራትንና የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለጻ እያደረገ ነው

You are currently viewing የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በእስካሁን ሂደት የተከናወኑ ተግባራትንና የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለጻ እያደረገ ነው

AMN ህዳር 30/2018

በመርሃ ግብሩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች፣ አምባሳደሮች፣ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በዚሁ ወቅት፤ ሀገራዊ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ዴሞክራሲን ለማስፈን በምክክር ላይ የተመሰረተ መፍትሔ ለማምጣት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ለዚህም ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሁሉም ድምጽ የሚሰማበት አካታችና አሳታፊ ሂደትን እየተከተለ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ተዓማኒነት ያላቸው አሰራሮችን በመከተል ሥራውን እያከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በሂደቱም አሳታፊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ በቆዩ ችግሮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ይበጃሉ የተባሉ አጀንዳዎች ልየታ ስራን እያጠናቀቀ መሆኑን ማስረዳታቸዉን ኮሚሽኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ስራው ውጤታማ እንዲሆን መስራት ሌላው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review