ሙስና የዴሞክራሲ ስርዓትን የሚያቀጭጭ፣ የሀገርን እድገት የሚጎትት ብልሹ አሰራር በመሆኑ ተግባሩን መታገልና መፀየፍ ይገባል

You are currently viewing ሙስና የዴሞክራሲ ስርዓትን የሚያቀጭጭ፣ የሀገርን እድገት የሚጎትት ብልሹ አሰራር በመሆኑ ተግባሩን መታገልና መፀየፍ ይገባል

AMN-ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም

የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቶ ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ ሙስና የዴሞክራሲ ስርዓትን የሚያቀጭጭ፣ የሀገርን እድገት የሚጎትት ብልሹ አሰራር በመሆኑ ተግባሩን መታገልና መፀየፍ እንደሚገባ የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ዓለም አቀፉ የፀረ ሙስና ቀን “ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ሀሳብ በህዳር ወር በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቶ ዛሬ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ፣ የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ፣ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፌዴራልና የክልል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽነሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ፣ ሙስና የዴሞክራሲ ስርዓትን የሚያቀጭጭ፣ የሀገርን እድገት የሚጎትት ብልሹ አሰራር በመሆኑ ተግባሩን መታገልና መፀየፍ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ትግሉን የተቀላቀለች ሀገር ብትሆንም፣ ተግባሩ እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ በብዙ መልኩ ውስንነት ነበረበት ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም፣ ኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ትግሉ ላይ የበኩሏን ስትወጣ ቆይታለች፣ ተግባሩን በተለይ ባለፉት ዓመታት ህጎችን በማውጣት ፣ የተቋማትን አገልግሎት በማዘመን፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን በማስፈን ለውጦችን እያመጣች ስለመሆኑ አንስተዋል።

ለአገልግሎት አሰጣጥ የእጅ መንሻ መጠየቅ፣ ከገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችና መሰል ጉዳዮች ለሙስና ትግሉ ተግዳሮት ሆነው ስለመቆየታቸውም ተመላክቷል።

በፅዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review