AMN ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም
በሞሮኮ በነበረው የንጉሥ ሙሀመድ 6ኛ የአፍሪካ ኡለማ ፋውንዴሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላበረከቱት አስተዋፆ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ ዕውቅና ሰጣቸው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው የልዑካን ቡድን በሞሮኮ ንጉስ መሐመድ 6ኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውኔዴሽን 7ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች አቀባበልና ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼኽ ሐሚዲ ሙሳ እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ምክር ቤት ባለፉት ሶስት አመታት በዲፕሎማሲው ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በ36 ሀገራት የኢትዮጵያ ኢስላማዊ እሴት እና ታሪኮችን ለአለም የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሼኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረድን በበኩላቸው፣ በሞሮኮ የነበረው ጉዞ ስኬታማ እና ከእስካሁኑ የተለየ ሀገራችንም ከፍ ያለችበት ነበር ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በሞሮኮ በነበራቸው ቆይታ የሀገራችን ታሪክ ከፍ ያለበት እና ኢትዮጵያ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት የተደረገበት እና በትብብር መስራት የሚቻልበት ውጤት የተመዘገበበት ነው ብለዋል።

በጉባኤው 48 ሀገራት የተሳተፉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር አብሮ የመስራት ዕድል ያገኘችበት ስለመሆኑ አብራርተዋል ።

በሞሮኮ በነበረው የንጉሥ ሙሀመድ 6ኛ የአፍሪካ ኡለማ ፋውንዴሽን ጠቅላላ ጉባኤ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በዳዕዋ እና ለእስልምና መጠናከር ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ከሞሮኮ ንጉሥ ሙሐመድ ስድስተኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን ሽልማት እንደተበረከተላቸው ተገልጿል።
በመሀመድኑር ዓሊ