የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ኮምፒዩተሮች እና ጄኔሬተሮች በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል እና ምቹ የመማር ማስተማሪያ ቦታዎችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎች ተስርተዋል፡፡
ተግባሩም ለትምህርት ጥራት ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በመቅርፍ የተማሪዎችን ውጤት አሻሻሏል፡፡

የክፍለ ከተማው ጽሕፈት ቤትም ይህንኑ ተግባር የሚያጠናክር ኮምፒውተር እና ጄኔነተር በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ድጋፉ ለትምህርት ስርዓቱ ትልቅ ዋልታ እንደሚሆን ገልጸው፣ ዘመኑን የዋጀ የትምህርት ስርዓት ለመዘርጋትም ያስችላል ብለዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር)፣ ከተማ አስተዳደሩ ለነገ ሀገር ተራካቢ ትወልድ ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ድጋፉም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ኮምፒዩተሮች እና ጄኔሬተሮች በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ መደረጉን የተናሩት ደግሞ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኸኝ አስታጥቄ ናቸው፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ከዚህ በፊት የኮምፒዩውተር እጥረት እንደነበረባቸው የገለጹት የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን፣ ድጋፉ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል እና በኦንላይን ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና አብርከቶው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ