ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የወላይታ ህዝብ ጥንታዊ ስልጣኔ መገለጫ፣ የበለፀገ ታሪክ እና ከህዝቡ ማንነት ጋር ስር የሰደደ ትስስር ያለው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው “ጊፋታ” በዩኔስኮ (UNESCO) በይፋ በመመዝገቡ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ጊፋታ ከአሮጌው ወደ አዲሱ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያበስር፤ እንዲሁም እርቅ እና ፍቅር የሚሰበክበት ታላቅ እሴት ነው።
“ጊፋታ” በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለሀገራችን የቱሪዝም ዕድገት ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም በላይ ድሉ ለመላው የወላይታ ህዝብ እና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ትልቅ ኩራት ነው:: በድጋሜ እንኳን ደስ አለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡