አርቲስት ኦሞ ሳንጋሬ፥ የግራሚ አዋርድ ሽልማት አሸናፊ፣ የአፍሪካ ሴቶች መብት ተከራካሪ እና ዓለም አቀፍ ዝናን የተጎናፀፈች ድምጻዊት ናት፡፡
በእናቷ በኩል “የኢትዮጵያ የደም ሐረግ እንዳላት” የምትናገረው ኦሞ ሳንጋሬ፥ የእንጦጦ ፓርክን ጨምሮ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም፣ የመንገድ መሰረተ ልማት፣ ፓርኮችን እና መሰል የልማት ስራዎችን ጉብኝት አድርጋለች፡፡

ኦሞ ሳንጋሬ በሰጠችው አስተያየትም “ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ከአምስት አመት በኃላ ነው። ባየሁተእ ለውጥ፣ በከተማዋ በፍጥነት መለወጥ እና በራሳችሁ አቅም ይህን የመሰለ ከተማና ጥራት ያለው ህንፃ መገንባታችሁ አስደንቆኛል” ብላለች።
ከከተማ ዕድገቱ ጋር የተሰሩ በርካታ ፓርኮችና የመዝናኛ ቦታዎች የሚደነቁ እንደሆነም አርቲስት ኦሞ ሳንጋሬ ተናግራለች።
በጉብኝቱ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ አርቲስቶች፣ ቲክቶኮሮች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችም ተሳትፏል።