ማንችስተር ሲቲ ሪያል መድሪድን ሲያሸንፍ ፣ አርሰናልም ድል ቀንቶታል

You are currently viewing ማንችስተር ሲቲ ሪያል መድሪድን ሲያሸንፍ ፣ አርሰናልም ድል ቀንቶታል

AMN ታህሣሥ 01 ቀን 2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ 6ኛ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሪያል ማድሪድን 2ለ1 አሸንፏል።

በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ በተደረገው ጨዋታ ኒኮ ኦራይሊ እንዲሁም ኧርሊንግ ሃላንድ በፍፁም ቅጣት ምት የሲቲን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

የማድሪድን ብቸኛ ግብ ሮድሪጎ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ውጤቱ ማንችስተር ሲቲን በ13 ነጥብ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ አድርጓል።

የሪያል ማድሪዱን አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶን ግን የበለጠ ጫና ውስጥ ከቷል። ከሜዳው ውጪ ክለብ ብሩዥን የገጠመው አርሰናል 3ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

ኖኒ ማዱኤኬ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማርቲኔሊ ሌላኛውን ግብ አስመዝግቧል። ብራዚላዊው የመስመር አጥቂ በአምስት ተከታታይ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

ስድስቱንም ጨዋታዎች በድል የተወጣው አርሰናል ቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር ለመግባት አንድ ነጥብ ብቻ በቂው ነው። የሰሜን ለንደኑ ክለብ በቀጣይ ኢንተር ሚላንን በሳን ሲሮ ይገጥማል።

በሌሎች ጨዋታዎች ጁቬንቱስ ፓፎስን 2ለ0 ሲያሸንፍ ፣ ናፖሊ በቤኔፊካ 2ለ0 ተረቷል። ባይር ሊቨርኩሰን ከ ኒውካስትል ዩናይትድ 2ለ2 ፣ አትሌቲክ ቢልባኦ ከ ፓሪሰን ዠርማ 0ለ0 ተጠናቋል።

ቦሩሲያ ዶርትመንድም ከቦዶ ያደረጉት ጨዋታ 2ለ2 አልቋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review