አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ስር ዋለ

‎AMN ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ‎ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህል ለመጫን የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ ያስታውቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review