ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ወጣት ሴቶች የነጻነት ምልክት እና የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
70 የሚደርሱ ወጣት ሴቶቹ የአፍሪካ ወጣት ሴቶች ማህበር አባላት ሲሆኑ አምስተኛውን ዓመታዊ አህጉራዊ ኮንቬንሽን (ACC) ለመታደም የመጡ መሆናቸው ተነግሯል።
ሁለተኛ ሀገራቸው እንዳሉ እንደተሰማቸው የገለጹት ወጣት ሴቶቹ በሙዚየሙ ባደረጉት ቆይታ እንደተደሰቱ መናገራቸዉን የአድዋ ድል መታሰቢያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያሳያል፡፡