ኢትዮጵያን ጥለው ከሻዕቢያ ጋር ሀገር ለመመስረት ከሚፈልገው ሐይሎች ጋራ መስራት አንፈልግም ሲሉ የአማራ ፍኖ ሕዝባዊ ድርጅት ( አፋሕድ) አመራሮች ተናገሩ፡፡
አመራሮቹ የሐይል አማራጭን የመረጡ ሌሎች አደረጃጀቶች ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጡም ጥሪ አቀርበዋል።
የአማራ ፍኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ምክትል የፖለቲካ መመሪያ ኃላፊ እና የወሎ ቤተ አማራ ጠቅላይ ግዛት እዝ የፖለቲካ ዘርፋ ኃላፊ እያሱ አበራ፣ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት እዝ የፋይናንስ ኃላፊ ከፍአለ አለሙ እና ወሎ ቤተ አማራ ጠቅላይ ግዛት እዝ የህዝብ አስተዳደርና የማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ ግርማ እጅግአየሁ ከመንግስት ጋር በተደረገዉ የሰላም ስምምነት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ስምምነቱ የሀገር አንድነትን የሚጠብቅ እና የሕዝቡን ጥያቄ የሚመልስ የሰላም ስምምነት አማራጭ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት መሸከም የለበትም ብለዋል አመራሮቹ።
ባለፉት ሶስት የትግል አመታት ለሕዝባችን የሰላም ምንጭ ሳይሆን የሰላም እጦት ምክንያት ሆነን ቆይተናል፣ ወደ ስምምነቱ የመጣነው የሰላም አካል ለመሆን ነዉ ሲሉ ተናግረዋል ።
ኢትዮጵያን ጥለው ከሻዕቢያ ጋር ሀገር ለመመስረት ከሚፈልገው ሐይሎች ጋራ መስራት አንፈልግም ብለዋል።
ከመንግሥት ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት አማራ ክልል ትምህርት የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ትምህርት እንዲጀምሩ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዳንኤል መላኩ