በትብብር ሥራችን ኢትዮጵያን ከዓለም ንግድ በማስተሣሠር ወደ ላቀ ብልጽግና እናሸጋግራለን

You are currently viewing በትብብር ሥራችን ኢትዮጵያን ከዓለም ንግድ በማስተሣሠር ወደ ላቀ ብልጽግና እናሸጋግራለን

AMN ታህሣሥ 02/2018 ዓ.ም

በትብብር ሥራችን ኢትዮጵያን ከዓለም ንግድ በማስተሣሠር ወደ ላቀ ብልጽግና እናሸጋግራለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ሀገራችን ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የምታደርገውን ጉዞና የድርድር ሂደት አስመልክቶ በተዘጋጀው ታላቅ መድረክ ተገኝተናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሥራች ብትሆንም፣ ከዓለም የንግድ ድርጅትና የትሥሥር ሂደት ለረጅም ጊዜ ባይተዋር ሆና ቆይታለች።

የመደመር መንግሥት በወሰደው ጠንካራ አመራርና ቁርጠኝነት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቻችን ከሁለት ዐሠርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የአባልነት የድርድር ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

በተለይም ባለፉት ሰባት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የድርድሩን መቋጫ የሚያሳዩ ናቸው።

የዓለም ንግድ ድርጅት አባል መሆናችን የገበያ ተደራሽነትን ያሰፋልናል፤ የንግድና ኢንቨስትመንት ግልጽነትና ተገማችነትን በማጎልበት ተመራጭነታችንን ያሳድጋል።

የድርድሩን ሂደት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ መንግሥት በቁርጠኝነት ይሠራል። ሂደቱ ቅንጅትን የሚሻ በመሆኑ የግሉ ዘርፍ፣ አስፈጻሚ ተቋማት ሚናቸውን እንዲወጡ ዓለም አቀፍ አጋሮችም ድጋፍቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚነኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review