ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል

You are currently viewing ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም

ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።

በቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ጥቅምን ማረጋገጥ እንደማይቻልም ተናግረዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ አብደላቲ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት በጽኑ አውግዘዋል።

ግብጽ ሰላም እና መረጋጋትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ አፍራሽ ንግግሮች እና ድርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባት ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በተጨማሪም ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል ብለዋል።

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ አቋም የተናጠል እርምጃ ነው ማለታቸው የዘመኑን እውነታ የማይመጥን የቅኝ ግዛት እሳቤ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ግብጽ በናይል ወንዝ እኔ ብቻ የበላይነቱን ልውሰድ የሚል ጊዜ ያለፈበት ትርክት ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸው መሰል እሳቤዎች ከሀገር ባለፈ ቀጣናዊ መረጋጋትን ስጋት ውስጥ የሚከቱ ናቸው ብለዋል።

አስተያየቱ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የሚቃረንና ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ መሆኑንም ተናግረዋል።

ግብጽ ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ ተላላኪ ቡድኖችን በመመልመል እና በማሰማራት እየደገፈች መሆኑን ገልጸው ይህን አካሄድ ኃላፊነት የጎደለውና ጠብ አጫሪ ድርጊት ሲሉም ገልጸውታል።

ከውሃ መብቶች እና ቀጣናዊ ትብብር አንጻር ሀሳባቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ የናይል ወንዝ አብዛኛው ድርሻ የምትወስደው ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ህጋዊ መብት እንዳላትም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕጋዊና በመርህ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን የኢትዮጵያ መብት እውቅና እየሰጠው እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ግብጽ በናይል ውሃ ላይ ብቻዬን ልጠቀም በሚል እያራመደች ያለችው አቋም ጊዜ ያለፈበትና የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ መሆኑን ጠቁመው ወቅቱ ከሚጠይቀው አስተሳሰብ እና አካሄድ ጋር የማይሄድ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review