አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መናገሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መናገሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው

AMN – ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መናገሻ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን 1ኛዉን የቱሪዝም ፎረም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ አዲስ አበባ የሰራቻቸዉ መሰረተ ልማቶች የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡

መዲናዋ ያላትን የቱሪዝም ፀጋዎች የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ 1ኛዉ የቱሪዝም ፎረም ከታህሳስ 5 እስከ 7/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ የገለጹት ኮሚሺነር ሁንዴ በፎረሙ ላይ ኤግዚቢሽን፣ የፎቶ አዉደ ርዕይ እና መሰል ሁነቶች ይደረጋሉ፡፡

ፎረሙ የመዲናዋን የቱሪዝም ፀጋ ማጉላት እና ግንዛቤንም የማስረፅ ግብን አላማ ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ዘመናዊ አሰራርን ከዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች ጋር አዋዶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ለፎረሙ ስኬታማነት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ ተናግረዋል

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review