አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የአዲስ አበባ ከተማ ስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን 22ኛውን የጸረ ሙስና ቀን ባከበረበት መድረክ ነው እውቅናውን ያገኘው።
እውቅናዉን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እጅ ተቀብለዋል።

ተቋሙ መዲናዋ በጸረሙስና እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘግብ ባከናወነችዉ ዉጤታማ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አበርክቶው ላቅ ያለ እንደነበርም ተገልጿል።
በተጨማሪም ብልሹ አሰራርን የሚያጋልጡ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ወደ ህዝብ እየደረሰ እንዳለም ተመላክቷል።

ከተማ አስተዳደሩ ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ረገድም ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀዉ 22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረሙስና ቀን በስኬት እንዲጠናቀቅም ዉጤታማ አስተዋፅኦ አድርጓል ተብሏል።

የፈደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአሁን ቀደም ባዘጋጀዉ የእዉቅና መርሃ ግብር ላይ ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከል ረገድ ከፍተኛ አበርክቶ ለነበራቸዉ ሶስት የሚዲያ ተቋማት እዉቅና የሰጠ ሲሆን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በመድረኩ ተሸላሚ እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡
በሃብታሙ ሙለታ