የሚዲያ አንቂዎች ሕግና ስርዓትን አክብረው ትውልዱ ላይ መሥራት ይገባቸዋል

You are currently viewing የሚዲያ አንቂዎች ሕግና ስርዓትን አክብረው ትውልዱ ላይ መሥራት ይገባቸዋል

AMN – ታኅሣሥ 3/2018 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለማረጋገጥ ከማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና ቲክቶከሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ የተካሄደው የማኅበራዊ ሚዲያ በኅብረተሰቡ አስተሳሰብ እና በሀገር ግንባታ ሒደት ላይ ያለውን ከፍተኛ ተጽዕኖ በመረዳት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል፡፡

ባለንበት የ“ድኅረ እውነት” ዘመን ሚዲያ አራተኛው የመንግስት አካል ሆኖ እንደሚያገለግል የገለጹት የቢሮዋ ኃላፊ አጠቃቀሙ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለትውልድ የማይጠቅሙ ሀሳቦችን ትቶ የሀገሪቱን አንድነት በሚያጠናክር መልኩ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በተደረገው ውይይት የተሳተፉ የማሕበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና ቲክቶከሮች በበኩላቸው፣ የትውልዱ አስተሳሰብ ላይ የተሻለ ንቃተ-ኅሊና ለመፍጠር እንደሚሠሩና ሀገራዊ እና የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ማኅበርም በቀጣይ በተሳሳተ አስተሳሰብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስታውቋል።

በውይይቱ ወቅት የቢሮው የሃይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ የማሕበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ከ”እኔነት” ይልቅ “እኛነት” ላይ በማተኮር ለቀጣዩ ትውልድ የሚጠቅም ይዘት መሥራት ላይ እንዲያተኩሩና ሕግና ሥርዓትን አክብረው እንዲሠሩ አሳስበዋል።

ፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review