በሕገ-ወጥ መንገድ ነዳጅ ሲቸረችር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing በሕገ-ወጥ መንገድ ነዳጅ ሲቸረችር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN – ታኅሣሥ 3/2018 ዓ.ም.

ከነዳጅ ማደያ አንድ ሊትር ቤንዚን በ129 ብር እየገዛ መልሶ አንዱን ሊትር በ200 ብር በድብቅ ሲሸጥ የነበረ ግለሰብን በትናንትናው ዕለት እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡

ዘሪሁን ኢብራሒም የተባለው ግለሰብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጡረታ ድልድይ በሚባለው አካባቢ የተያዘው ሲሆን በራሱ የሕንጻ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ ውስጥ አራት ባለ 20 እና ስድስት ባለ 25 ሊትር ጀሪካን እንዲሁም ሀያ ሶስት ባለ 2 ሊትር ቤንዚን በእናቱ መኖሪያ ቤት ውስጥ አከማችቶ እንደተገኘ ነው የፖሊስ መምሪያው የገለጸው፡፡

የነዳጅ ግብይት በሕገ-ወጥ መልኩ መፈጸም የሕግ ተጠያቂነት የሚያስከትል ድርጊት ከመሆኑ ባሻገር ነዳጅ በቀላሉ የሚቀጣጠል ነገር በመሆኑ ከማደያ ውጪ ማከማቸት ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review