በፈረንጆቹ 2027 በኢትዮዽያ የሚካሄደዉን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (COP32) በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ብቻ 150 ያህል ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት በማከናወን ተመራጭ መዲና መሆኗን የገለጹት ከንቲባዋ በዘንድሮዉ ዓመት ብቻ እስካሁን 105 የተለያዩ ኮንፍረሶችና ዓለም አቀፍ ኩነቶች ተካሂደዋል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ከከተማዋ ባለሀብቶች፣ የሆቴል፣ የሪልስቴት፣ የቱሪዝም፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና አጠቃላይ የአገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ጋር ጉባዔውን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማካሄዳቸውን በመግለጽ ግብረ ኃይል በማቋቋምም የሥራ ክፍፍል መደረጉን አሳውቀዋል።
በቀጣይም ቅድመ ዝግጅቶች እየተገመገሙ ከምንጊዜውም የተሻለና ደማቅ ጉባዔ ለማካሄድ በቅንጅት እንደሚሠሩ ከንቲባዋ ገልጸዋል።