አርሰናል ወደ ድል ለመመለስ ወልቭስን ይገጥማል

You are currently viewing አርሰናል ወደ ድል ለመመለስ ወልቭስን ይገጥማል

AMN ታህሣሥ 04 ቀን 2018 ዓ.ም

አርሰናል የተደላደለ የሚመስለው መሪነቱ በመጠኑ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።

የማንችስተር ሲቲ ተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ፣ የአርሰናል ደግሞ ከሦስት የመጨረሻ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ማሸነፍ በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለውን ልዩነት ወደ ሁለት ነጥብ አጥብቦታል።

የፔፕ ጋርዲዮላን ቡድን አስፈሪ አመጣጥ ለመመከት አርሰናል ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። በበርካቶች ግምት የዛሬው ጨዋታ ወደ ድል የሚመለስበት ግጥሚያ ይሆናል።

ከዚያ ቅስም ሰባሪ የአስቶንቪላው ሽንፈት ለማገገም የሚጥሩት መድፈኞቹ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ነው ከወልቭስ ጋር የሚጫወቱት። አርሰናል ወልቭስን በገጠመባቸው የመጨረሻዎቹ አምስት ጨዋታዎች ሁሉንም አሸንፏል።

ከ15 የሊጉ ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ ያገኘው ወልቭስ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ አርሰናልን ማሸነፍ የቻለው በሦስት አጋጣሚዎች ብቻ ነው። ዛሬ በሚደረገው የ16ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብርም የማሸነፍ አቅም ያለው አይመስልም።

በጨዋታው በአርሰናል በኩል ዊሊያም ሳሊባ ፣ ዩሪያን ቲምበር ፣ ዴክለን ራይስ እና ሊአንድሮ ትሮሳርድ መግባታቸው አልተረጋገጠም። ተከላካዮቹ ጋብርኤሌ ማጋሌሄሽ እና ክሪስቲያን ሞስኬራ ከጉዳታቸው ለመመለስ ሳምንታት ይፈልጋሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review