በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ቀንሷል

You are currently viewing በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ቀንሷል

AMN – ታሕሳስ 4/2018 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ተከትሎ በከተማዋ በተተገበሩት ዘመናዊ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና የመረጃ አያያዝ በትራፊክ አደጋ የሚከት የሞት መጠን በእጥፍ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ የዲጂታል ሥርዓትን በመተግበር የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ካሏት የተሽከርካሪዎች ቁጥር 80 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት በአዲስ አበባ ከተማ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ በከተማ ከሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ በ5ቱም የከተማ መውጫና መግቢያ በሮች በሚከሰተው የትራፊክ ፍሰት ከተማዋ ተጨማሪ የትራፊክ መጨናነቅን ሲፈጥር መቆየቱንም አንስተዋል።

መንገዶቹም ሆኑ የነበሩት መሰረተልማቶች ፕላናቸውን ጠብቆ ያልተገነቡ በመሆናቸው እንዲሁም ከ4መቶ በላይ የሚሆኑ የመገጣጠሚያ አደባባዮች ኋላቀር መሆን ችግሩን አስፍተውት እንደነበር ተናግረዋል።

አሁን ላይ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉት ለቁጥጥር የተመቹ ዘመናዊ የአስፋልት መንገዶች ከተማዋ ይበልጥ የተሳለጠ እና የተደራጀ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር ስርዓት መፈጠሩን ተግረዋል፡፡

በከተማ ወስጥ የሚንቀሳቀሱ ተከርካሪዎች፣ የተለያዩ ማሽኖች፣ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የተለያየ የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን የግዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመሰራታቸው ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review