የኪነ – ጥበብ ፈጠራ ስራዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ ተገለጸ።
በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የማሕበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኪ – ጥበብ ስራዎች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር እና በሀገር ጉዳይ በጋራ ለመቆም ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ከክልል እና ከፌዴራል የተውጣጡ የኪነ – ጥበብ ፈጠራ ባለሙያዎች፣ የክልል የባህል እና በኪነ – ጥበብ ዘርፍ ኃላፊዎች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ በኪነ – ጥበብ ፈጠራ ስራዎች እና ብሄራዊ ጥቅምን በተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡

የኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ ፈጠራዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያረጋግጡ መሆኑ ይገባቸዋል ብለዋል።
ሀገር አንድ ናት ፣ ፓርቲዎች ብዙ ናቸው ፣ ሁላችንም እናልፋለን በመሆኑም ሀገር ይቀጥላል የኪነ ጥበብ ስራዎች በሙሉ የሀገርን አንድነት እና ሕብረት መጠበቅ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል ሚኒስትር ድኤታው።
አዲስ ሲኒማ ማዕከል ፣ ኮፊ ፓርክ ፣ አራዳ ፓርክን እና ሙያ ኢትዮጵያ የዕደ ጥበብ ስራዎች ማምረቻ ማህበርን እና በእንጦጦ የሚገኘውን የሰርከስ ሴንተር ከክልል እና ከፌዴራል የተውጣጡ የኪነ – ጥበብ ባለሙያዎች እና የክልል የባህል እና የኪነጥበብ ዘርፍ ኃላፊዎች መጎብታቸው ይታወሳል ።
በዳንኤል መላኩ