“የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ቱሩፉቶች ”በሚል መሪ ሀሳብ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ህዝባዊ ውይይት መካሄድ ጀምሯል፡፡
መንግስት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጀሞ ወረዳ 13 እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት፣ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱልሀኪም አባቡልጎ፣ ውይይቱ ያስፈለገው ባለፉት ዓመታት ያሳካናቸው የልማት ስኬቶችን ለማፅናት፣ ጉድለቶችንም ለመለየት እና ለማስተካከል የጋራ የልማት አቅጣጫንም ለመተለም ነው ብለዋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የጥናትና ሱፐርቪዥን ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን ግዛው፣ “የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ቱሩፋቶች”’በሚል መሪ ሀሳብ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል::
በውይይቱ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ወጣቶች እና ሴቶች እንዲሁም የክፍለ ከተማው እና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::
በየሺዋስ ዋለ