”የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስሥት ትሩፋቶች!” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ሕዝባዊ ውይይት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደርም ቀጥሏል።
ውይይቱ በሐገር ሽማግሌዎች የሐይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎችና ሀደ ስንቄዎች በፀሎትና በምስጋና ተከፍቷል።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የጉለሌ እፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ጉተማ ሞረዳ (ኢ/ር) ፣ውይይቱ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም አስተዳደሩ መሰል ሕዝባዊ ውይይቶች ሲያካሂድ የቆየ መሆኑን አስታውሰው፣ መድረኩ ተለዋዋጭ በሆነው ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ወዲህ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።
ለዚህም ስኬቶች የከተማ አስተዳደሩ አመራር ከነዋሪው ጋር በጋራ በቅንጅት በመሰራቱ የተመዘገበ ድል መሆኑን አስታውሰዋል።
የክፍለ ከተማው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የብልፅግና ፖርቲ ምክትል ኃላፊ አቶ ሲሳይ ኬኔ ሕዝባዊ ውይይቱ ነዋሪው የሚያነሳቸውን ችግሮች በአግባቡ ለመለየት እና
ለመፍትሔው አብረን ለመሰሰራት ያስችለናል ብለዋል።
በመድረኩ ለውይይት የተዘጋጀ ሰነድ እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ሰነዱን መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
በታምሩ ደምሴ