ባንኩ የባለ አክሲዮኖች 4ተኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን፣ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2025 በጀት ዓመት የሰራቸውን ስራዎች የሚገልጽ ሪፖርት ለጉባኤው አቅርቧል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ሁሴን ሀሰን (ዶ/ር)፣ አሁን ያለው የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ መጠንም 7.1 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ይህም ካለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ የ3.8 ቢልየን ብር ወይም የ92.5 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ ላይም ሰፋፊ ስራዎችን በማከናወን በበጀት ዓመቱ የ4.33 ቢልየን ብር ዝውውር ያደረገ ሲሆን፣ የሞባይል ባንኪንግ ደምበኞቹንም 114 ሺህ 695 ማድረሱን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የባንኩ አጠቃላይ ባለ አክሲዮኖችም 31 ሺህ 518 መድረሳቸውን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በቶማስ አሊጋዝ