ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአገር ባለውለታዎች ለሆኑ እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ የከተማችን ነዋሪዎችን ለይተን በእጣ አስተላልፈናል ።
ከህዝብ ጋር ባደረግነው ውይይት የተሰጡንን ጥቆማዎች ተጠቅመን ባደረግነው ማጣራት የለየናቸውን ነዋሪዎቻችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ በማበስ እና ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ስራ ተከናውኗል ።

በተለይም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ ለተነሳችሁ፣ በሶስተኛ ወገን ክርክር ምክንያት ስትንገላቱ የቆያችሁ ዛሬ ችግሩን ፈተን የመኖሪያ ቤት ስላገኛችሁ እጅግ ደስተኞች ነን፤ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልፀዋል ፡፡