የአፍሪካ ዋንጫ ለአፍሪካውያን ኩራታቸው በመሆኑ የአውሮፓ ክለቦች ሊያከብሩት ይገባል ፦ዴቪድ ሞይስ

You are currently viewing የአፍሪካ ዋንጫ ለአፍሪካውያን ኩራታቸው በመሆኑ የአውሮፓ ክለቦች ሊያከብሩት ይገባል ፦ዴቪድ ሞይስ

AMN ታህሣሥ 04 ቀን 2018 ዓ.ም

የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ “የአፍሪካን ዋንጫ ሙሉ በሙሉ መከበር አለበት” በማለት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

የአፍሪካን ዋንጫ ማክበር አለብን ያሉት ሞይስ ተጫዋቾቹ ለሀገራቸው ክብር ሊፋለሙ ወደ ውድድሩ ሲሄዱ ሊደገፉ ይገባል በማለት ገልጸዋል።

ተጨዋቾች ወደ መድረኩ ስፍራ መሄዳቸው ትክክል ነው ምክንያቱም “AFCON ለተጫዋቾቹ ከውድድር በላይ በመሆኑ በጉጉት ይጠብቁታል ፤ ለዚህም ቀና አስተሳስብ በአሰልጣኞች እና በክለብ ኃላፊዎች ያስፈልጋል” ብለዋል።

የአፍሪካ ዋንጫ ለአፍሪካውያን ተጫዋቾች ኩራት፣ ማንነት፣ ፍቅር እና ትሩፋታቸው በመሆኑ ክለቦች በደስታ ሊመለከቱት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኤቨርተን ሞሮኮ በምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ እድሪሳ ጋና ጌ እና ኢሊማን ንዲያዬ የመሳሰሉ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ወደ ውድድሩ ይሸኛል።

በአንዱዓለም ስማቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review