ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች አዳምጦ ተገቢ ምላሽ መስጠት የብልፅግና ፓርቲ መገለጫ ነው

You are currently viewing ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች አዳምጦ ተገቢ ምላሽ መስጠት የብልፅግና ፓርቲ መገለጫ ነው

AMN – ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም

በመዲናዋ በሚገኙ 119 ወረዳዎች “የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግስት ቱሩፋቶች” በሚል መሪ ሀሳብ፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙርያ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ከዚህ በፊት በማዕከል እና በክፍለ ከተማ ደረጃ ህዝባዊ ውይይቶች መደረጋቸው የሚታወስ ነው።

በዛሬው እለትም በመዲናዋ በሚገኙ በ119 ወረዳዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙርያ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይ መድረኩ ላይ ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች አዳምጦ ተገቢ ምላሽ መስጠት የብልፅግና ፓርቲ መገለጫ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ባለፉት የለውጥ አመታት መንግስት ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ በመስራቱ የኢትዮጲያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ስኬታማ ስራዎች ተከናውነዋል ተብሏል።

በዚህም የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ስራዎች በመስራት አዲስ አበባ ከተማን የዓለም የስህበት ማዕከል፣ ለነዋሪዎቿ ውብና ፅዱ ከተማ እንዲሁም የዓለም የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከተማ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።

በእነዚህ የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ሰፋፊ ስኬቶች ህዝብና መንግስት ተመካክረው እና ተናበው በመስራታቸው የመጡ ውጤቶች መሆናቸውንም በውይይቱ ተገልጿል።

የዛሬው የውይይት መድረክ ዓላማም ከህዝብ ጋር በመወያየት የሚነሱ ሀሳብና አስተያየቶችን ለቀጣይ እቅድ እንደመነሻ በመጠቀም ለሀገገር ከፍታ ከህዝብ ጋር በቅንጅት ለመስራት እንደሆነም ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከማህበረሰቡ ለሚነሱ ለልማት እና ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥም ተገልጿል። መረጃው የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነው ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review