በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየራቸው ባለፈ የነዋሪውን ህይወት ቀይረዋል

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየራቸው ባለፈ የነዋሪውን ህይወት ቀይረዋል

AMN – ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየራቸው ባለፈ የነዋሪዎችን ህይወት የቀየሩ መሆናቸውን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ነዋሪዎቹ የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች በሚል በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ላይ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና የቤት አቅርቦት መጨመር ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

ባለፉት ጊዚያት ነዋሪዎች ላነሱት ጥያቄ የተሰጡ ምላሾችና የቀጣይ ትኩረቶች ላይ ያተኮረው የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የህዝብ መድረክም በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች ተካሂዷል፡፡

በወረዳ 2 አስተዳደር በተካሄደው ውይይት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ ባለፉት የለውጥ አመታት የተሰሩ ስራዎች የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ያጎሉ የነዋሪዎቹን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሰው ተኮር ስራዎች መሆናቸውን ተሳታፊዎቹ አንስተዋል፡፡

መንግስት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር እና ሀገርን ከድህነት ለማውጣት የጀመራቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት የውይይቱ ተሳታፊዎች ለተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስኬትም የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በህዝብና በመንግስት ትብብር የተሰሩት የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የጠየቁት ተሳተፊዎች የኑሮ ውድነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር፣ምርት የሚደብቁና አላግባብ ዋጋ የሚጭምሩ ነጋዴዎችን መቆጣጠር፤የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይዳ አወል በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ መንግስት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ከዚህ በፊት ያልተለመዱ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ አቅርቦትን ለማሳደግ የተለያዩ አማራጮችን በመዘርጋት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀይማኖት እንየው በበኩላቸው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ከተማ አስተዳደሩ የገበያ አማራጮችን የማስፋት ስራ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም የገበያ ተደራሽትን የማስፋት፣ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ እና የንግድ ስርዓቱን መቆጣጠር ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review