የውሃ አቅርቦትን ማሳደግና በአገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚገባ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ

You are currently viewing የውሃ አቅርቦትን ማሳደግና በአገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚገባ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ

AMN – ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም

የውሃ አቅርቦትን ማሳደግና በአገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚገባ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ሳምንት መካሄድ የጀመረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ በወረዳ ደረጃ ተካሂዷል፡፡

ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ነዋሪዎች የተሳፉበት የውይይት መድረኩ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ተካሂዷል፡፡

ነዋሪዎቹም በከተማዋ በመንግስት የተሰሩ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ያሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

መንግስት የጀመራቸው የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የጠየቁት ነዋሪዎቹ በውሃ አቅርቦትና በአገልግሎት ዘርፍ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ማረም እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

ከነዋሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች እና ችግሮችን በቀጣይ የእቅድ አካል በማድረግ እንደሚሰራም ሃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበበ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጸሃይ ኪባሞ ብልሹ አሰራርን ለመቀረፍ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውሰዋል፡፡

በቀጣይም ብልሹ አሰራርን ለመቀርፍ እና አግልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጀመሩ ስዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጸሃይ ኪባሞ ገልጸዋል፡፡

የውሃ አቀርቦትን ለማሻሻል ባለፉት 7 አመታት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ሃላፊዋ በቀጣይም የውሃ አቅርቦቱን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review