በወለጋ ዞኖች ሰላምን በማጽናት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት አምጥተዋል

You are currently viewing በወለጋ ዞኖች ሰላምን በማጽናት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት አምጥተዋል
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም

የዉይይት መድረኩ ተሳታፊዎችም የለውጡ መንግስት ለአካባቢው በሰጠው ትኩረት ሰላም ለማፅናትና የልማት ስራዎችን ለማከናወን ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

በዞኑ ባላፉት ዓመታት አጋጥሞ የነበረው የጸጥታ ችግር ተወግዶ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በዚህ ወቅት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መንግስት ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባ ያሰሙት ብስራቶች የሚሳካው በህዝቡ የተደራጀ ተሳትፎ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታትም በግብርና፣ በመንገድ፣ በትምህርትና በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስትር መሀመድ ኢድሪስ፣ መንግስት በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለአካባቢው ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ መስፍን መላኩ፤ በአካባቢው ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ ህዝቡ ሰላሙን በማጽናት ስራዎቹ ቀጣይ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሷቸው ጥያቄዎችም ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review