በደብረ ብርሃን ከተማ ዝርፊያና እገታ ሲፈጽሙ የነበሩ 60 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing በደብረ ብርሃን ከተማ ዝርፊያና እገታ ሲፈጽሙ የነበሩ 60 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN – ታኅሣሥ 5/2018 ዓ.ም.

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደብረ ብርሃን ከተማ “የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በከተማዋ ዝርፊያ፣ እገታና በነጻነት የመንቀሳቀስ ችግሮች ይስተዋሉ እንደነበር ገልጸው ከነዋሪው ጋር በትብብር በተሠራ ሥራ ባለፉት 3 ወራት ብቻ ከ60 በላይ አጋችና ዘራፊ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን ተከትሎም በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን መቻሉን ከንቲባው አብራርተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተደድር አቶ ማስረሻ በላቸው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ማዕከሏ ደብረ ብርሃን ከተማ መንግስት ለጀመረው ለውጥ ማሳያ መሆን ጀምራለች ብለዋል።

አማራ ክልል የጠላትን ዓላማ በያዙ ኃይሎች የጦርነትና የግጭት ማዕከል እንዲሆን ቢፈለግም ሕልማቸው ሳይሳካ ቀርቶ በክልሉ በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተደድሩ።

በመድረኩ የከተማዋ ነዋሪዎች የተለያዩ የልማትና የመልካም አስዳደር ጥያቄዎች አንስተው ውይይት እየተደረገበት ነው።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review