የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ከሚያስተዳድራቸው ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ ያስገነባውን ለመድኃኒት መሸጫ፥ ማከማቻና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ሕንጻ ሥራ አስጀምሯል፡፡
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና “ከነማ በአዲስ ጎዳና” በሚል ያስጀመረው ቅርንጫፎችን ለማብዛት፥ አቅርቦትን ለማሳደግና የነዋሪውን ፍላጎት ለማርካት እየሠራ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ሠይፈ ደምሴ በሕንጻ ምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡
42 ዓመታትን ያስቆጠረውና አንጋፋው የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በሚፈለገው ልክ አገልግሎት እንዲሰጥ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተንኩዌይ ጆክ በተለይ ደኅንነታቸው የተጠበቁ መድኃኒቶችንና የሕክምና ቁሳቁሶችን ለኅብረተሰቡ ማቅረብ እንዲሁም ዲጂታል አሠራርን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመሥጠት እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጸሚ ካባ መብራቱም ነዋሪው በአቅራቢያው የመድኃኒት አቅርቦት እንዲያገኝ ሲያነሳ ለቆየው ጥያቄ ከነማ ፋርማሲዎች ምላሽ በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በአንዋር አሕመድ