“የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሐሳብ ህዝባዊ ውይይት በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሴ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል በቀጣይ በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የልማት ሥራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።
መንግስት ባለፉት ዓመታት በግብርና፣በቱሪዝም፣ በኢንደስትሪ፣ በአይ.ሲ.ቲ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በትኩረት ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለምአየሁ አሠፋ በበኩላቸው የሕዝብን ድምጽ መስማትን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ ከሁለቱ አመራሮች በተጨኣሪ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረህማን፣ የአፋር ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን፥ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በውይይት መድረኩ ላይ ለሕዝባዊ ውይይት መነሻ የሆኑ ጽሑፎች ቀርበው በተሳታፊዎች ሀሳብ እና አስተያየቶች እየተሰጡባቸው ይገኛሉ።
በሀብታሙ ሙለታ