ዎልቭስ ሦስቱንም የጨዋታው ግቦች ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል አሸነፈ

You are currently viewing ዎልቭስ ሦስቱንም የጨዋታው ግቦች ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል አሸነፈ

AMN ታህሣሥ 05 ቀን 2018 ዓ.ም

በሜዳው ኤምሬትስ ዎልቭስን ያስተናገደው አርሰናል 2ለ1 አሸንፏል።

ግልፅ የግብ ዕድል ለመፍጠር የተቸገረው አርሰናል የዎልቭሱ ግብ ጠባቂ ሳም ጆህንስቶን እና ተከላካዩ ሙስኬራ በራሳቸው ግብ ላይ ያስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሦስት ነጥብ አስገኝተውለታል።

የወልቭስን ግብ ቶሉ አሮኮዳሬ ማስቆጠር ችሏል። በጨዋታው የተቆጠሩ ሦስቱንም ግቦች የዎልቭስ ተጫዋቾች አስቆጥረዋል።

መድፈኞቹ ድሉን ተከትሎ ዛሬ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከሚጫወተው ማንችስተር ሲቲ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት በማስፋት መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከ16 ጨዋታ 36 ነጥብ ማግኘት ችሏል።

ዘጠኝ ተከታታይ የሊግ ጨዋታ የተሸነፈው ዎልቭስ ሁለት ነጥብ ብቻ በመያዝ የደረጃው ግርጌ ላይ ተቀምጧል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review