የታጠቁ ኃይሎች ሀሳባቸውን ወደ አዳራሽ ይዘው እንዲመጡ መንግስት ጥረቱን እንዲቀጥል የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ

You are currently viewing የታጠቁ ኃይሎች ሀሳባቸውን ወደ አዳራሽ ይዘው እንዲመጡ መንግስት ጥረቱን እንዲቀጥል የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ

AMN- ታህሳስ 5/2018 ዓ.ም

በደብረ ብርሃን ከተማ “የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በከተማዋ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ያደነቁት ነዋሪዎቹ ሊሰሩ ይገባል ያሏቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችም አንስተዋል።

በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ሕዝብን ለከፋ ችግር ዳርጓል ያሉት ነዋሪዎቹ ይሄም ሊበቃ ይገባል ብለዋል።

በጫካ ያሉ የታጠቁ ሃይሎች ሀሳባቸውን ወደ አዳራሽ ይዘው እንዲመጡ መንግስት ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የኑሮ ውድነት ከፍ ማለት ፣ ሕዝብን ያማረሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መኖር ፣ ለወጣቶች የተፈጠረው የሥራ እድል ዝቅተኛ መሆን በነዋሪዎቹ የተነሱ አንኳር ጥያቄዎች ናቸው።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ብልሹ አሠራርን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል አስተዳደሩ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አንስተዋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ሕዝብ አስተካክሉ የሚለንን ለማስተካከል ነው ውይይቱን ያደረግነው ብለዋል።

የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከል ፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የገበያ ስርዐቱን በህግ መምራት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።

ሰላምን ለማረጋገጥ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተደድር አቶ ማስረሻ በላቸው ናቸው።

በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ ያቀረቡት ምክትል ርዕሰ መስተደድሩ የከተማዋ ነዋሪዎች የሰላም ጥረቱን እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review